የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

አቶ ዳንኤል ዳምጠው አንጭሶ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በክልሉ ጠንካራ ፣ ተወዳዳሪ እና ዘመናዊ የንግድ ስርዓት ለመፍጠር ተቋሙ የተሰጠውን ተልእኮ አንግቦ ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ተቋሙ ከተመሰረተ 2ዓመት ያልሞላው ቢሆንም ቢሮውን ከከማደራጀት አንስቶ ባጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስራዎች ተሰርተው ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡፡ በተለይም ቢሮው ዘመናዊ የግብይት ስርዓትን ለመዘርጋት በሚሰራቸው ስራዎች በተቋሙ የሚሰጠው የንግድ ፈቃድና እድሳት አገልግሎት ደንበኞች ባሉበት ሆነው ስልኮቻቸውን በመጠቀም አገልግሎቱን በኦንላይን እንዲያገኙ በክልሉ 93 ኦንላይን አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን አቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ያሉ ህገ-ወጥ አሰራሮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል የእለታዊ የነዳጅ መመዝገቢያ ኦንላይን ሲስተም ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ 

ተቋሙ በተለይም የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ ባከናወናቸው ተግባራት 134 የሰንበት ገበያዎችን በክልሉ በተለያዩ ከተሞች ያቋቋመ ሲሆን በገበያዎቹ ምርቶች በዓይነት፣ በመጠን እና በተመጣጣኝ ዋጋ ይቀርባሉ፡፡ ከሰንበት ገበያዎች በተጨማሪ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንሼቲቭ “ከሰንበት እስከ ሰንበት” በሚል መሪ ቃል በሁሉም ቀናት ግብይት የሚደረግባቸው ደረጃቸውን የጠበቁ ገበያዎችን ማቋቋም ተችሏል፡፡ በዚህም ህብረተሰቡ ተጠቃሚነቱን በተለያየ አጋጣሚ እየገለፀ የሚገኝ ሲሆን ቢሮውም ገበያዎችን ከማቋቋም ባለፈ የግብይት ስርዓቱ ለታለመለት አላማ ብቻ እንዲውል ድጋፍና ክትትል እያደረገ... ተጨማሪ