የእርሻ ምርቶች ግብይትና ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት
ማለት የእርሻ ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያ የገበያ ትስስር የመፍጠር፣ የህግ ማዕቀፍ ለወጣላቸው የሰብል ምርቶች ጥራትና ህግ ወጥ ዝውውር የመቆጣጠር፣ በወልና በኮንትራት እርሻ ለተሰማሩ ባላሃብቶች ኤክስፖርት እንዲያደርጉ ድጋፍ በመስጠት አምራቹና ሸማቹን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያከናውን ሂደት ነው፡፡
ዳይሬክቶሬቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
- የእርሻ ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያ የገበያ ትስስር የመፍጠር አገልግሎቶች፤
- ህግ ማዕቀፍ ለወጣላቸው የሰብል ምርት ጥራትና የመቆጣጠር አገልግሎት፤
- በወልና በኮንትራት እርሻ ለተሰማሩ ባላሃብቶች ኤክስፖርት እንዲያደርጉ ድጋፍ የማድረግ አገልግሎት፤
- የግንዛቤ ማስጨበጫና የስልጠና አገልገሎት፣
- የመረጃና ምክር አገልግሎት፣
- የግብይት ሕግ ማዕቀፍ ዝግጅት፤
- የተለያዩ ፕሮጄክት ዝግጅትና ክትትል
- ህግ ማዕቀፍ ለወጣላቸው የእርሻ ምርቶች ጥራት ማረጋገጫ መስጠት፣
- ህግ ወጥ የእርሻ ምርቶች ዝውውር የመከታተልና ሥራ ማካሄድ፤